ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ስለውጭ ሀገር መሪዎች የተናገሩት ፤

ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ስለውጭ ሀገር መሪዎች የተናገሩት ፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን እንደተናገሩት ከተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መቼ እንደሚገናኙ አላወቁም ፤ ከትራምፕ ጋር ካወሩ አራት አመት እንዳለፋቸው ጨምረው ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ሁልጊዜም ትራምፕን ለማናገር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ከቱርክ አቻቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጋር ቋሚ የሆነ ግንኙነት አላቸው። ፕሬዚዳንት ፑቲን የቀድሞ የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ  ሞስኮ ከገቡ በኋላ እንዳላገኟቸው ፤ ነገርግን የማግኘት እቅድ እንዳላቸው ታውቋል። ሶሪያ ውስጥ የጠፋውን አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ጉዳይ አል-አሳድን ለመጠየቅ ፕሬዝዳንቱ ቃል ገብተዋል። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቻይናን ፕሬዝዳንት ሺ ዢፒንግ ጓደኛዬ ብለዋቸዋል። አሁን ላይ ከማን ጋር መቆየት ትወዳለህ ተብለው የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ፑቲን ጓደኞቹን በተደጋጋሚ ማግኘት እና እነርሱ ጋር ሻይ እየጠጡ ማውራት ያስደሰተኛል ብለዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ ተሳትፎ ያደረጉትን ፖለቲከኞቹን ኮል፣ ቺራክ እና ቤርለስኮኒን በስም ጠርተው እንደሚያደንቋቸው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0