ሩሲያ በሶሪያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በሶሪያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበች በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኒቤንዚያ በሶሪያ ላይ በተቀመጠው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር "ሁሌም እንደምንለው የሚጎዳው ተራው ሕዝብ ስለሆነ፤ ማዕቀቡ መነሳት አለበት" ብለዋል። ሩሲያ ለወንድም የሶሪያ ህዝብ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ ጠቁመዋል። ሀገሪቱን መልሶ ለመገንባት እንዲቻል የአውሮፓ ሕብረት በሶሪያ ላይ የጣለውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ በድጋሚ ሊመለከት ይገባል ሲሉ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌየን ረቡዕ እለት ተናግረዋል። "ለመልሶ ግንባታ መሳለጥ በሶሪያ ላይ የተጣሉ የዘርፍ ማዕቀቦችን እንደገና ማጤን አለብን፤ ይህንን ለማድረግ እውነተኛ የሆነ አካታች የፖለቲካ ሂደት ማየት አለብን" ብለዋል ቮን ዴር ሌየን ስትራስቡርግ ውስጥ ባደረጉት ነግግር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0