የሩሲያ እና የኬንያ እናቶች በናይሮቢ የእግር ኳስ ጨዋታ ማድረጋቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀከሁለት ሀገራት የተውጣጡ አራት ቡድኖች በጨዋታው ላይ እንደተሳተፉ ኤምባሲው ገልጿል።“እንዲህ አይነት ውድድሮችን ቀደም ሲል በቻይና፣ በካዛክስታን እና በቤላሩስ አካሂደናል፤ አሁን ደግሞ ከአፍሪካ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ወስነናል። ለእኛ የመጀመሪያው ምርጫ ኬንያ ነበረች፣ ማለትም የናይሮቢ የተጨናነቁ ሰፈሮች፤ በዚህም መሰረት በእግር ኳስ ፍላጎት ካላቸው እናቶች እና ሴት ልጆቻቸው ጋር ግጥሚያ አዘጋጅተናል። ይህ ለእኛ ከሌላ ሀገር ዜጎች ተወካዮች ጋር ወዳጅነትን ለመመሥረት እና ሁለቱ ሀገሮች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ለመርዳት የሚያስችል መንገድ ነው፤ የእግር ኳስ ዲፕሎማሲ ዓይነት ነገር ነው” ሲሉ "ፉትቦል ማምስ" የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት መስራች የሆኑት ኤልቪራ ሌስኒቻያ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።በዚህም ሶስት የኬንያ አሸናፊ ቡድኖች የማስታወሻ ሽልማቶችን ማለትም- ባለ ዜብራ ሜዳሊያዎች፣ ኩባያዎችን ፣ በኮክህሎማ ቅርጽ የተቀቡ ኔስቲንግ ዶል ( እናትነትን የሚያንፀባርቁ አሻንጉሊት መክተቻዎች) እና የእንጨት ማንኪያዎችን መረከባቸውን በኬንያ የሩሲያ ኤምባሲ ገልጿል። በኤምባሲው መረጃ መሰረት የኬንያ ተጫዋቾቹ ወደፊቱ በሩሲያ እንዲጫወቱ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20241205/14923.html
የሩሲያ እና የኬንያ እናቶች በናይሮቢ የእግር ኳስ ጨዋታ ማድረጋቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ
የሩሲያ እና የኬንያ እናቶች በናይሮቢ የእግር ኳስ ጨዋታ ማድረጋቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
የሩሲያ እና የኬንያ እናቶች በናይሮቢ የእግር ኳስ ጨዋታ ማድረጋቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀከሁለት ሀገራት የተውጣጡ አራት ቡድኖች በጨዋታው ላይ እንደተሳተፉ ኤምባሲው ገልጿል።“እንዲህ አይነት ውድድሮችን ቀደም ሲል በቻይና፣ በካዛክስታን እና በቤላሩስ... 05.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-05T10:02+0300
2024-12-05T10:02+0300
2024-12-05T10:34+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሩሲያ እና የኬንያ እናቶች በናይሮቢ የእግር ኳስ ጨዋታ ማድረጋቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ
10:02 05.12.2024 (የተሻሻለ: 10:34 05.12.2024)
ሰብስክራይብ