ኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ዘርፏን ለማሳደግ የብሪክስ ትብብርን እንደምትሻ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ገለፁ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ዘርፏን ለማሳደግ የብሪክስ ትብብርን እንደምትሻ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ገለፁ በብሪክስ ስብስብ ውስጥ አዲስ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ የቡድኑን እውቀት ተጠቅማ የህዋ ሳይንስ ግቦቿን ለማሳካት እንደምትሻ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህሩ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና የጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተባባሪ አባል የሆኑት ዶክተር ጌትነት አያኔ ተናግረዋል። በቅርቡ በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 10ኛው የብሪክስ የስነ-ፈለክ ስራ ቡድን ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ዶ/ር አያኔ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ከሌሎች የብሪክስ ሃገራት ጋር በዘርፉ ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል። "ከዚህ ስብሰባ ብዙ እንጠብቃለን" ያሉትት ዶ/ር አያኔ "ከተቀሩት የብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ትብብር እንፈጥራለን ብለን እንጠብቃለን። በተለይ በቴክኖሎጂ፣ ሳይንስ እና ፈጠራ የበለጠ ለመስራት የተሻለ የሰው አቅም እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የተጀመሩ በርካታ ውጥኖች እንዳሉ የጠቆሙት ተወካዩ የኢትዮጵያን የጠፈር ሳይንስ ፕሮግራም “አንድ እርምጃ ወደፊት” የመውሰድ ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል። ዶ/ር አያኔ በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ተመራማሪዎች መካከል ያለውን ትብብርም ያነሱ ሲሆን በምርምርና ምልከታ እንዲሁም በጋራ የምርምር ሥራዎች የተማሪዎች ልውውጥ ፕሮግራም እንዳላቸው ጠቁመዋል። "በዚህ ወርክሾፕ ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዱ ታዋቂ ፕሮፌሰር ሲሆኑ ለጋራ የምርምር ስራ ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ጎብኝተዋል። ከዚህ ወርክሾፕ በኋላም ከሩሲያ ጋር የተሻለ ትብብር ይኖረናል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0