ኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ቀንን በምታከብርበት ዕለት ለአንድነት እና ለሉዓላዊነት ጠንክሮ መስራት እንደሚባ ጥሪ ቀርበ ትላንት እሑድ ጳጉሜ 3 ሀገራዊ ነፃነት እና ሉአላዊነትን በሁሉም የሥራ መስኮች ማሳካት ያለውን ጠቀሜታ ለማጉላት "የሉዓላዊነት ቀን" ተብሎ ተከብሯል።በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው የፓናል ውይይት እና አውደ ርዕይ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ሉአላዊነት ለማስከበር በህብረት መቆም እንዳለበት ጠንከር ያለ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ፣ የቴክኖሎጂ፣ የእውቀት እና የበጀት ነፃነትን ማስከበር ያለውን አስፈላጊነትን ገልፀው፤ እውነተኛ ነፃነት ከእርዳታ ጥገኛም ሆነ ከኋላ ቀርነት ጋር የተላቀቀ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ታሪካዊ ፋይዳ በማጉላት የሀገሪቱን ለዘመናት ያስጠበቀችው ነፃነት እና የዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ወራሪዎች ላይ የተቀዳጀው ድል የሉዓላዊ ነፃነት ማሳያ ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም የምግብ ሉዓላዊነት የብሄራዊ ነፃነት ምሰሶ መሆኑን አስምረውበታል። የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ቀንን በምታከብርበት ዕለት ለአንድነት እና ለሉዓላዊነት ጠንክሮ መስራት እንደሚባ ጥሪ ቀርበ
ኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ቀንን በምታከብርበት ዕለት ለአንድነት እና ለሉዓላዊነት ጠንክሮ መስራት እንደሚባ ጥሪ ቀርበ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ቀንን በምታከብርበት ዕለት ለአንድነት እና ለሉዓላዊነት ጠንክሮ መስራት እንደሚባ ጥሪ ቀርበ ትላንት እሑድ ጳጉሜ 3 ሀገራዊ ነፃነት እና ሉአላዊነትን በሁሉም የሥራ መስኮች ማሳካት ያለውን ጠቀሜታ ለማጉላት "የሉዓላዊነት ቀን" ተብሎ... 09.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-09T15:15+0300
2024-09-09T15:15+0300
2024-09-09T15:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ቀንን በምታከብርበት ዕለት ለአንድነት እና ለሉዓላዊነት ጠንክሮ መስራት እንደሚባ ጥሪ ቀርበ
15:15 09.09.2024 (የተሻሻለ: 15:44 09.09.2024)
ሰብስክራይብ