ግብፃዊው አርኪኦሎጂስት ዛሂ ሀዋስ የነፈርቲ ቅርሶችን ለማስመለስ ፊርማ እያሰባሰበ ነው

ሰብስክራይብ
ግብፃዊው አርኪኦሎጂስት ዛሂ ሀዋስ የነፈርቲ ቅርሶችን ለማስመለስ ፊርማ እያሰባሰበ ነው የነፈርቲ ቅርሶች በአሁኑ ጊዜ በበርሊን ኒውስ ሙዚየም ውስጥ ይገኛል። እ.ኤ.አ በ1912 በቴል ኤል-አማርና በጀርመን አርኪኦሎጂካል ቡድን የተገኘው ሲሆን ትክክለኛ መገኛውን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ሲያከራክ ቆይቷል። ሀዋስ ቅርሱ ከግብፅ በህገ ወጥ መንገድ የተወሰደ በመሆኑ ወደ መገኛ ሀገሩ እንዲመለስ ሲሟገት ከርሟል።ሀዋስ ዘመቻው በውጪ የሚገኙ ሁሉንም የግብፅ ቅርሶች ማስመለስ ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን በተለይ ሶስት ቁልፍ ቅርሶች ፤ ወደ መገኛቸው መመለስ ላይ ያተኩራል ያለ ሲሆን እነሱም የነፈርቲቲ ቅርስ፣ የሮሴታ ስቶን እና የዴንደራ ዞዲያክ ላይ ያተኮረ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቶ ተናግሯል።ደጋፊዎች ወደ ድረ-ገጹ በመግባት ፊርማቸውን እንዲፈርሙ ፤ ይህም ባህላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ቅርሶች እንዲመለሱ ዓለም አቀፍ ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ አሳስቧል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0