የፑቲን እና የሱቢያንቶ ስብሰባ ቁልፍ ንግግሮች

ሰብስክራይብ
የፑቲን እና የሱቢያንቶ ስብሰባ ቁልፍ ንግግሮች የአዲስ ተመራጩ የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት፡- ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማዳበር ያለውን ፍላጎት አረጋግጠዋል። የሀገራችን "ታላቅ ወዳጅ " ሲሉ ሩሲያን ጠርተው፤ ሩሲያ በኢንዶኔዥያ ኢኮኖሚ ውስጥ የበለጠ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርግ ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሩሲያ ወታደራዊ ልዑካንን እ.አ.አ በህዳር 2024 በሚደረገው የመከላከያ ኤግዚቢሽን ላይ እንዲገኝ ግብዣ አቅርበዋል።  ከሩሲያው ኩባንያ ሮሳቶም ጋር በኒውክሌር መስክ ላይ ሽርክና ለመፍጠር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡- ተመራጩ ፕሬዝዳንት(የወደፊት አቻቸው) የሩሲያ ወዳጅ መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል የመከላከያ ግንኙነት እንደሚኖር ተናግረዋል ። በሞስኮ እና በጃካርታ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲሚቀጥል እና ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ያላቸውን ተስፋ ገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0