የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከግድያ ሙከራ መትረፋቸው ተዘግቧል

ሰብስክራይብ
የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከግድያ ሙከራ መትረፋቸው ተዘግቧልበምስራቅ ሱዳን የቀይ ባህር ግዛት በሚገኘው የገበይት ወታደራዊ ተቋም በነበረው የወታደራዊ አካዳሚ ተማሪዎች ምረቃት ስነስርዓት “ አጥፍቶ ጠፊ ” አል-ቡርሃንን ኢላማ አድርጎ እንደነበር የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ዘገባዎቹ አክለውም የሱዳኑ መሪ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና ወደ ሀገሪቱ ጊዜያዊ መዲና ፖርት ሱዳን መወሰዳቸውን ዘገባው አክሎ ገልጿል።የሱዳን ጦር በመግለጫው እንዳስታወቀው በገበይት ከተማ የአየር መከላከያ ሰራዊት በበአሉ ላይ ያነጣጠሩ ሁለት የድሮኖች ጥቃት በማድረሱ አምስት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጿል።ጥቃቱ የተሰነዘረው እ.አ.አ ከ ሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽን ሃይሎች (RSF) መካከል እየተካሄደ ያለውን ግጭት መነሻ በማድረግ ነው።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0