የሐምሌ 24 ቀትር ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 24 ቀትር ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የሐማስ ፖሊት ቢሮ ሃላፊ እስማኤል ሃኒዬህ ማክሰኞ ምሽት በሰሜናዊ ቴህራን ልዩ ወታደራዊ መኖሪያ ላይ በተፈጸመ "የአየር ድብደባ" መሞታቸውን ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። በሃኒዬ ግድያ ሳቢያ በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ የንቅናቄው ቃል አቀባይ ተናገሮ፤ የሃኒዬ መሞት በሃማስ አመራር ላይ ተጽእኖ እንደማይኖረው አክለው ተናግረዋል።🟠 ሩሲያ ሶስተኛውን ደረጃ ስትራቴጂካዊ ያልሆኑ የኒውክሌር መሳሪያ ልምምዶች ጀምራለች ሲል የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ 19 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሲያ ክልል ላይ በአንድ ጀንበር መመታታቸውን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 እ.አ.አ ሀምሌ 29 በእንግሊዝ ሳውዝፖርት ከተማ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተቀስቅሶ ነበረ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው አንድ ታዳጊ በከተማው በሚገኝ የዳንስ ስቱዲዮ ውስጥ ገብቶ በቢላዋ የሶስት ህፃናት ህይወት መቅጠፉን ተከትሎ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች አመላክተዋል።🟠 ሩሲያዊው ተጓዥ ፌዮዶር ኮኑሆቭ በሰሜን ዋልታ ያደረገውን መንሳፈፍ አጠናቅቋል። ኮኑሆቭ 20 ቀናት ከ22 ሰአት ከ45 ደቂቃ በበረዷማው ሥፍራ ብቻውን በማሳለፍ የአለም ክብረወሰን አስመዝግቧል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0