የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 የምሽት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 የምሽት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የኢራን ተመራጭ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን የለውጥ አራማጁን ፖለቲከኛ ሞሀማድ ሬዛ አረፍን የሀገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ሩሲያ በልዩ ወታደራዊ ዘመቻዋ የበላይነት በመያዟ ምዕራባውያን እና ዩክሬን የድርድር መግለጫዎችን እንደ ታክቲካል እርምጃ በመጠቀም እረፍት ለማግኘት እና ሃይላቸውን ለመመለስ እየተጠቀሙበት እንደሆነ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ተናገሩ። 🟠 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ የደኅንነት ቡድን አባላት እና የሚስጥራዊ አገልግሎት ኤጀንቶች ቶማስ ማቲው ክሩክስ ፔንስልቬንያ በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ መተኮስ ከመጀመሩ በፊት አጠራጣሪ የነበሩ ሁኔታዎችን የአካባቢው ፖሊስ ሪፖርት ሳያደርግ ቀርቷል በማለት በግል ቅሬታቸውን እያሰሙ እንደሆነ ምንጮችን አጣቅሰው ምእራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 አሜሪካ እና ጃፓን ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ኦፕሬሽን እዝ ሊያቋቁሙ እንደሆነ አስታውቀዋል። 🟠 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እሁድ እለት ከአሜሪካ ጉብኝታቸው ቀደም ብለው ወደ እስራኤል የተመለሱ ሲሆን በጎላን ተራራ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም ወደ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ማቅናታቸውንም ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0