በደቡባዊ አፍሪካ በክፍለ ዘመን አንድ ጊዜ የሚከሰት እጅግ የከፋ ድርቅ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበ

ሰብስክራይብ
በደቡባዊ አፍሪካ በክፍለ ዘመን አንድ ጊዜ የሚከሰት እጅግ የከፋ ድርቅ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበ “በጣም የከፋው ጊዜ አሁን እየመጣ” እንደሆነ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የደቡብ አፍሪካ ክልል ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሎላ ካስትሮ ለኤ.ኤፍ.ፒ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። "ሰዎች ምንም ነገር መሰብሰብ አልቻሉም፤ ችግሩ የሚቀጥለው አዝመራ በሚያዚያ 2025 መድረሱ ብቻ ነው" ብለዋል። አንዳንድ ግምቶች ድርቁ በ100 ዓመት ውስጥ ክልሉን የሚያጠቃ አስከፊው ድርቅ እንደሆነ ያመለክታሉ ሲሉም ተናግረዋል ዳይሬክተሯ። በርካቶች ህልውናቸው ግብርና ላይ በወደቀበት ክልል ቢያንስ 27 ሚሊዮን ሰዎች በድርቅ ተጠቅተዋል ያሉት ካስትሮ ድርቁ በዛምቢያ 70% እና በዚምባቡዌ 80% የሚሆነውን ምርት አጥፍቶ አቅርቦትን በከፍተኛው እንደቀነሰ እና የምግብ ዋጋ ንረት እንዳስከተለ አስታውቀዋል። ምንም እንኳን የኤልኒኖ ዑደት ቢያበቃም ተፅዕኖው አሁንም ቀጥሏል። በአንዳንድ ሀገራት ደግሞ የድርቅ ወቅት ቀደም ብሎ እንደጀመረ ካስትሮ ተናግረዋል። "ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ነው" ያሉት ካስትሮ "ስለ ድርቅ ወይም ረሃብ ማውራት ባንችልም ሰዎች ግን በቂ ምግብ መግዛት ወይም በቀን የሚያስፈልጋቸውን የካሎሪ መጠን ማግኘት አይችሉም። ህጻናት እየቀጠኑ ይመጣሉ፤ የህዝቡ ስቃይም ይጀምራል" ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0