ዩክሬን እና ምዕራባውያን ኤፍ-16 ተዋጊ ጀቶች በጦር ሜዳው ላይ ለውጥ ማምጣታቸውን እንደሚጠራጠሩ አንድ ሪፖርት ገለፀ

ሰብስክራይብ
ዩክሬን እና ምዕራባውያን ኤፍ-16 ተዋጊ ጀቶች በጦር ሜዳው ላይ ለውጥ ማምጣታቸውን እንደሚጠራጠሩ አንድ ሪፖርት ገለፀ "ለብዙ ግዜ ሲጠበቁ የነበሩት ኤፍ-16 ተዋጊ ጀቶች በሳምንታት ውስጥ በዩክሬን ይበራሉ፤ ነገር ግን በአንድ ወቅት ኪዬቭ ጨዋታ ቀያሪ ስትል የገለፀቻቸው እነዚህ ጀቶች በጦር ግንባሩ ላይ ፈጣን ለውጥ መፍጠራቸው አጠራጣሪ እንደሆነ የዩክሬን እና ምዕራባውያን ባለስልጣናት ማስጠንቀቃቸውን” ሪፖርቱ አስነብቧል። ለዚህ ምክንያቱ የተዋጊ ጀቶቹ ቁጥር አንስተኛ መሆን እና የሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር የአየር መከላከያ ዘዴዎች እንደሆነ ሪፖርቱ አክሏል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ እና የኔቶ ጭፍራዎቿ ከሩሲያ ጋር የቀጥታ ግጭት ሊከቱ የሚችሉ አደጋዎችን እየፈጠሩ እንደሆነና ይህም አስከፊ መዘዝ እንደሚያስከትል ቀደም ሲል አስጠንቅቋል። ኪዬቭ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መሸከም የሚችሉ F-16 ተዋጊዎችን ማግኘት መቻሏ ሩሲያ ኒውክሌር ካላቸው ምዕራባውያን ሀይሎች ስጋት እንደተደቀነባት አድርጋ ትቆጥረዋለች ሲልም አሳስቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0