የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገት፦ በ2030 ለአፍሪካ 3.

ሰብስክራይብ
የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገት፦ በ2030 ለአፍሪካ 3.3 ሚሊዮን የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል ኤፍኤስዲ አፍሪካ እና ሾርትሊስት የተሰኙ ድርጅቶች “በአፍሪካ የአረንጓዴ ስራዎች ትንበያ” በሚል ርዕስ የወጣው ሪፖርት እንደ ታዳሽ ሃይል፣ ኢ-ሞቢሊቲ፣ ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ባሉ ዘርፎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሰለጠኑ ስራዎችን የመፍጠር አቅም እንዳለ አሳይቷል። ጥናቱ የሚያተኩረው በአምስት ቁልፍ ሀገራት ማለትም በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ሲሆን ከአህጉሪቱ የአረንጓዴ ስራ እድገት ከ20% በላይ ይሸፍናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሪፖርቱ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገትን ለማንቀሳቀስ የሰው ሀይል ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት ሰጥቷል። 60% የሚሆኑት አዳዲስ ስራዎች የሰለጠነ የሰው ሃይል የስራ መደቦች ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ይህም ለመካከለኛው መደብ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል። "የሰው ሃይል እና ብቃት ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገት ግብአትነት ጠቃሚ ነው የሚለውን እምነት በአግባቡ የተመለከተ የመጀመሪያው ሪፖርት ነው" ሲሉ ሾርትሊስት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፖል ብሬሎፍ ተናግረዋል። የታዳሽ ሃይል ዘርፍ ትልቁ የስራ እድል ፈጣሪ ይሆናል ተብሎ ሲገመት የፀሃይ ሃይል ብቻ ለ1.7 ሚሊዮን ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። የውሃ ሃይል በተለይም በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎም ይጠበቃል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0