የሐምሌ 19 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 19 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ዴሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ካማላ ሃሪስ ጷግሜ 5 ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመከራከር ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀው ነገር ግን የቀድሞ ፕሬዝዳንት "ሃሳባቸውን እየቀያየሩ" ነው ሲሉ ከሰዋቸዋል። የትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ሰራተኞች ዲሞክራቶች በይፋ እጯቸውን እስኪመርጡ ድረስ ከሃሪስ ጋር ክርክር ለማድረግ እንደማይስማሙ ተናግረዋል።🟠 ኢራቅ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰፈር የአየር ማረፊያ የሚሳኤል ኢላማ መሆኑን የሻፋክ ኒውስ ፖርታል ዘገባ አመልክቷል።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሃይሎች 6 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በሩሲያ ሮስቶቭ እና ኩርስክ ክልሎች ላይ መተው ጥለዋል።🟠 ከ628,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ቻይና በተከሰተው የአውሎ ንፋስ አደጋ ዞን ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ። የቻይና ሴንትራል ቴሌቪዥን እንደዘገበው የፉጂያን ግዛት ባለስልጣናት 150,000 ነዋሪዎችን ከአደገኛ አካባቢዎች አውጥተዋል።🟠 የሩሲያ የፌዴራል ሜዲካል-ባዮሎጂካል ኤጀንሲ ስፔሻሊስቶች ለኤች.አይ.ቪ ኢንፌክሽን ሕክምና ሁለት አዳዲስ ክትባቶችን በመስራት ላይ ናቸው፡፡ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0