የቫልዳይ መድረክ በታንዛኒያ፦ የአዲሱ ዓለም ስርዓት ተሳታፊዎች ህጋቸውን እራሳቸው ይቀርፃሉ ረቡዕ እለት በሞስኮ የሚገኘው ታዋቂ ቲንክ ታንክ ቫልዳይ የውይይት ክለብ “ሩሲያ-አፍሪካ፡ የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም የትብብር ስትራቴጂ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን የሩሲያ እና አፍሪካ ኮንፈረንስ እካሂዷል። ኮንፍረንሱ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካ ውስጥ ዳሬሰላም ታንዛኒያ ተካሂዷል። "በጣም ወሳኙ ነገር ይህ ስርዓት እንኳን ሳይሆን አሁን ላለንበት ግዜ አዲስ አውድ መሆኑ ነው" ሲል የቫልዳይ የውይይት ክለብ የምርምር ዳይሬክተር እና የሩሲያ መጽሔት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዋና አዘጋጅ ፌዮዶር ሉክያኖቭ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተናግሯል። ሩሲያዊው ባለሙያ አክሎም "የዓለም ስርዓት አንዳንድ ህጎችን ማውጣት አለበት ብለን ደምድመናል፤ ነገር ግን አዲሶቹ ተጫዋቾች እነዚህን ህጎች ከራሳቸው በስተቀር ማንም እንዲያወጣ ፍላጎት እንደሌላቸው እንመለከታለን።" "የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ረጅም ታሪክ አለው። እና በዚህ አዲስ ዘመን ለዚህ ተሰማሚ እና ተለዋዋጭ ከባቢ ሁኔታ ምስጋና ይግባና የእያንዳንዱን ሀገራት ለዕድገታቸው የተረጋጋ አቅም የማስቀጠል ግብ በመከተል ሙሉ ለሙሉ አዲስ እና ፈጠራ የታከለበት ነገር የማምጣት እድል አለን” ብለዋል። በውይይቱ 40 የሚደርሱ ሩሲያውያን እና አፍሪካውያን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የኮንፈረንሱ ዓላማ ፍትሃዊ የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም እና የንግድ ግንኙነቶችን የመገንባት አቋም ላይ "መመሳሰል" መፍጠር ነው። የኮንፈረንሱ ውጤት አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው ሶስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት መሰረት እንደሚሆን አዘጋጆቹ ተስፋ አድርገዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240725/6193.html
የቫልዳይ መድረክ በታንዛኒያ፦ የአዲሱ ዓለም ስርዓት ተሳታፊዎች ህጋቸውን እራሳቸው ይቀርፃሉ
የቫልዳይ መድረክ በታንዛኒያ፦ የአዲሱ ዓለም ስርዓት ተሳታፊዎች ህጋቸውን እራሳቸው ይቀርፃሉ
Sputnik አፍሪካ
የቫልዳይ መድረክ በታንዛኒያ፦ የአዲሱ ዓለም ስርዓት ተሳታፊዎች ህጋቸውን እራሳቸው ይቀርፃሉ ረቡዕ እለት በሞስኮ የሚገኘው ታዋቂ ቲንክ ታንክ ቫልዳይ የውይይት ክለብ “ሩሲያ-አፍሪካ፡ የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም የትብብር ስትራቴጂ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን... 25.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-25T17:00+0300
2024-07-25T17:00+0300
2024-07-25T17:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የቫልዳይ መድረክ በታንዛኒያ፦ የአዲሱ ዓለም ስርዓት ተሳታፊዎች ህጋቸውን እራሳቸው ይቀርፃሉ
17:00 25.07.2024 (የተሻሻለ: 17:20 25.07.2024)
ሰብስክራይብ