ሩሲያ እና ሊቢያ የኤኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያለመ ሰፋ ያለ ስምምነት ተፈራረሙ በሩሲያ የንግድና ኢንዱስትሪ ማኅበራት ምክትል ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ባዳልኮ እና የሊቢያ የንግድ ማኅበራት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሙሃመድ አል-ራይድ የተፈረመው አዲሱ ስምምነት ሞስኮ ውስጥ ነው የተጠናቀቀው። የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነው። ስምምነቱ የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ ቁልፍ ተግባራትን ይዘረዝራል 🟠 የመረጃ ልውውጥ፦ የገበያ እድሎችን እና የኢንቨስትመንት ተስፋዎችን በተመለከተ የጋራ መረዳት አንዲኖር የኢኮኖሚ እና የንግድ መረጃዎችን መጋራት።🟠 የጋራ ዝግጅቶች፦ የሁለቱን ሀገራት ነጋዴዎች እና ኢንቨስተሮችን ለማገናኘት የኢኮኖሚ መድረኮችን፣ ኮንፈረንሶችን እና ስብሰባዎችን ለማዘጋጀት ድጋፍ ማድረግ።🟠 መደበኛ ግምገማዎች፦ የትብብር ሂደቶችን ለመከታተል እና የጋራ ግቦችን የሚያደናቅፉ መሰናክሎችን ለማስወገድ በየጊዜው ምክክሮችን ማካሄድ።🟠 ስትራቴጂካዊ ውይይቶች፦ በሩሲያ እና ሊቢያ መካከል ወቅታዊ እና የወደፊት የሁለትዮሽ ትብብር መንገዶችን መመልከት። ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በአስቸጋሪ የፖለቲካ ሁኔታዎች ውስጥ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ፍላጎት እያሳዩ ባለበት ወቅት የመጣ ነው። ፊርማው የሊቢያ ባለስልጣናት ከሞስኮ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው በቅርብ ግዜያት ከተናገሩ በኋላ የመጣ እንደሆነም ታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240725/6173.html
ሩሲያ እና ሊቢያ የኤኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያለመ ሰፋ ያለ ስምምነት ተፈራረሙ
ሩሲያ እና ሊቢያ የኤኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያለመ ሰፋ ያለ ስምምነት ተፈራረሙ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ሊቢያ የኤኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያለመ ሰፋ ያለ ስምምነት ተፈራረሙ በሩሲያ የንግድና ኢንዱስትሪ ማኅበራት ምክትል ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ባዳልኮ እና የሊቢያ የንግድ ማኅበራት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሙሃመድ አል-ራይድ የተፈረመው አዲሱ... 25.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-25T12:46+0300
2024-07-25T12:46+0300
2024-07-25T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ሊቢያ የኤኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያለመ ሰፋ ያለ ስምምነት ተፈራረሙ
12:46 25.07.2024 (የተሻሻለ: 13:20 25.07.2024)
ሰብስክራይብ