የሐምሌ 17 ረፋድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 17 ረፋድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዋና መሥሪያ ቤት የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ካማላ ሃሪስ ለባይደንን ምርጫ ቅስቀሳ ተመድቦ የነበረውን ገንዘብ ተቀብለዋል በማለት ቅሬታ ማቅረባቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።🟠 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በላኦስ ከሚካሄደው የአሲያን(ASEAN) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን በርካታ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን እንደሚያካሂዱ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።🟠 ትላንት ሌሊት የሩሲያ አየር መከላከያዎች በቤልጎሮድ ክልል ላይ ሶስት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መምታቱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።🟠 የ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የሩሲያን ማዕከላዊ ባንክ ሃብት ላልተወሰነ ጊዜ ለማገድ ባቀረበው ሀሳብ ላይ ለመወያየት ዛሬ እንደሚገናኙ ፋይናንሺያል ታይምስ አንድ መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል።🟠 በፎክላንድ ደሴቶች የኖርዌይ የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ተጋጭቶ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን የስፔን የዜና ወኪል ኢኤፍኢ ዘግቧል። ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የስፔን ዜጐች መሆናቸው ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0