ዛምቢያ በ2027 አጠቃላይ የመዳብ ምርቷን በ40 በመቶ ለመጨመር እቅድ ይዛለች

ሰብስክራይብ
ዛምቢያ በ2027 አጠቃላይ የመዳብ ምርቷን በ40 በመቶ ለመጨመር እቅድ ይዛለችበአፍሪካ ሁለተኛዋ የመዳብ አምራች የሆነችው ዛምቢያ በ2023፤ 700,000 ቶን የነበረውን የመዳብ ምርቷን በ40 በመቶ በማሳደግ ወደ አንድ ሚሊዮን ቶን ለማድረስ ውጥን ይዛለች።ይህንን ትልቅ ዓላማ ሀገሪቱ ከ2025-2027 የመካከለኛ ጊዜ የበጀት እቅድ ውስጥ የተቀመጠ እና በሁሉን ዓቀፍ ስልት የሚሳካ ይሆናል። ይህም በዋና ዋና ማዕድን ማውጫዎች ላይ ያሉ ችግሮችን መፍታት፣ አዲስ በተገኙ የማዕድን ማውጫዎች ላይ ምርትን መጀመር እና በነባር የማዕድን ማውጫዎች ላይ ያለውን ምርት ማሳደግን ያካትታል።እ.ኤ.አ በ2022 የሀገሪቱ የመዳብ ምርት በአስራ አራት አመታት ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፤ ፣ይህም በዋናነት በማዕድን ላይ የሚጣለው ቀረጥ መለዋወጥ እና ከቀድሞ መንግስት ጋር በተፈጠረው ግጭት እንደነበር ተገልጿል።መዳብ ለአለም አቀፍ የኃይል ሽግግር ወሳኝ ማዕድን ሲሆን ዛምቢያ ወደ ውጭ ከምትልከው ገቢ 70 በመቶ ድርሻ ይይዛል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0