የአፍሪካ ህብረት ባህልን ለመጠበቅ እና የአህጉሪቱን ልማት ለማሳደግ የሰው ሰራሽ አስተውህሎ (AI )ስትራቴጂን ይፋ አደረገ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ህብረት ባህልን ለመጠበቅ እና የአህጉሪቱን ልማት ለማሳደግ የሰው ሰራሽ አስተውህሎ (AI )ስትራቴጂን ይፋ አደረገ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት በጋና አክራ ባካሄደው 45ኛው መደበኛ ስብሰባ የሰው ሰራሽ አስተውህሎ (AI )እና የአፍሪካ ዲጅታል ኮምፓክት ስትራቴጂን አጽድቋል። ስትራቴጂው አፍሪካዊ ማንነት፣ ባህል እና ክብር ለመጠበቅ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስፋፋት እና ኢ-ሥነ ምግባራዊ አጠቃቀምን ለመከላከል የአርቴፊሻል አስተውሎን ለመጠቀም ያለመ ነው። የአፍሪካ ህብረት የመሠረተ ልማት፣ ኢነርጂ እና ዲጂታይዜሽን ኮሚሽነር አማኒ አቡዘይድ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት አፍሪካ ሰው ሰራሽ አስተውህሎ ላይ ያላትን አቋም ግልጽ ለማድረግ  ስትራቴጂው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደቀረበ ተናግረዋል። ስትራቴጂዎቹ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0