የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ በቀን 550,000 የነዳጅ ምርት በማጣራት ወደ ትልቅ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው

ሰብስክራይብ
የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ በቀን 550,000 የነዳጅ ምርት በማጣራት ወደ ትልቅ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው የናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ የተቀመጠውን ግብ ሊያሳካ ይችላል፤ ነገር ግን በሀገር ውስጥ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባን ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴ። በቀን 650,000 በርሜል ነዳጅ የማጣሪያ አቅም ያለው ፋብሪካ ከመንግሥታዊው የነዳጅ ድርጅት ኤን ኤን ፒ ሲ ከሚጠብቀው 15 የድፍድፍ ጭነቶች ውስጥ፤ አምስት ድፍድፍ ጭነቶችን ብቻ እየተቀበለ መሆኑን ገልፆ፤ ይህም የብራዚል እና የአሜሪካን ድፍድፍ ነዳጅ በደላሎች በኩል በበርሜል 4 ዶላር በመጨመር እየገዙ መሆኑን ተናግረዋል። ቀደም ሲል መንግሥታዊው የነዳጅ ድርጅት ኤን ኤን ፒ ሲ በቀን 300,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለማቅረብ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፤ ነገርግን ከአነስተኛ ምርት ሳቢያ እና ድፍድፍ ነዳጅን በማጣራት ወደ ቤንዚን ለመለዋወጥ እየሠራ መሆኑን እንቅፋት እንደሆነበት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0