እስራኤል በየመን የወደብ ከተማ ላይ በፈፀመችው ጥቃት 2 ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ምንጮች ገልፀዋል።

ሰብስክራይብ
እስራኤል በየመን የወደብ ከተማ ላይ በፈፀመችው ጥቃት 2 ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ምንጮች ገልፀዋል። “በአል ሁዳይዳህ ላይ በተፈጸመ የአየር ድብደባ 2 ሰዎች ሲገደሉ፤ 3 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል” ሲል የሃውቲ የደህንነት ምንጭ ለስፑትኒክ ተናግሯል። እስራኤል በየመን የሁቲ ኢላማዎች ላይ የፈፀመችው የመጀመሪያ የአየር ድብደባ ነው። ሁቲዎች በበኩላቸቸው እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እስክትቆም ድረስ በቀይ ባህር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እንደሚፈፅሙ አስታውቀዋል። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ ቅዳሜ ዕለት እንደተናገሩት እስራኤል በምዕራባዊው የመን የወደብ ከተማ አል ሁዳይዳህ ላይ የፈጸመችው ጥቃት “በኢራን የሚደገፈውን የሽብር ድርጅት” ሽንፈት ያሳያል ብለዋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢራን ላይ የሚጣለውን ማዕቀብ እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0