የዩክሬን ጦር ካሚካዜ ሰው አልባ አውሮፕላኑ የሩሲያን የእሳት አደጋ መኪና ሆን ብሎ ሲያጠቃ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቀቀ

ሰብስክራይብ
የዩክሬን ጦር ካሚካዜ ሰው አልባ አውሮፕላኑ የሩሲያን የእሳት አደጋ መኪና ሆን ብሎ ሲያጠቃ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቀቀ የዩክሬን ድሮኖች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ክልል የመኪና እሳት የማጥፋት ተልእኮ በተሰጠው የአደጋ ጊዜ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰራተኞች መኪና ላይ እሮብ እለት ሁለት ጊዜ ተኩሰዋል። የክልሉ የሩሲያ የአደጋ ጊዜ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዲፓርትመንት ሰራተኞቸ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጿል። "በጦር ሜዳው ላይ ውድቀቱን የተገነዘበው የዩክሬን መከላከያ ሃይል ሆን ብሎ የነፍስ አድን ሰራተኞችን በማጥቃት 'ድሉን' በበይነመረብ ለጥፏል። ይህ ለተባበሩት መንግሥታት የዓለም ፍርድ ቤት የኪዬቭን ኢሰብአዊነት እና ወንጀል የመፈፀም ፍላጎት የሚያረጋግጥ ነው" ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0