ሜታ የናይጄሪያን ህግ በመጣስ 220 ሚልየን ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት የሀገሪቱ የሸማቾች ኮሚሽን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ሜታ የናይጄሪያን ህግ በመጣስ 220 ሚልየን ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት የሀገሪቱ የሸማቾች ኮሚሽን አስታወቀ ኮሚሽኑ በፌስቡክ* እና ዋትስአፕ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መረጃ የሚጋራበትን መንገድ መርመሮ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ "የመጨረሻው ውሳኔ ሁለት መቶ ሃያ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር (220,000,000.00) የገንዘብ ቅጣት እንደጣለ" ገልጿል። ሜታ* የናይጄሪያ ተጠቃሚዎችን መረጃ ያለፍቃዳቸው ተጠቅሟል፣ የገበያ የበላይነቱን ያላግባብ ተጠቅሟል፣ ናይጄሪያውያንን ተመሳሳይ ህግ ካላቸው ሌሎች ሀገራት በተቃራኒ በአድሎአዊ እና እኩልነት በጎደለው መንገድ አስተናግዷል ብሏል ጋዜጣዊ መግለጫው። *ሜታ እና ፌስቡክ በሩሲያ በአክራሪ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ታግደዋል ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0