ከ140 በላይ ስደተኞችን በስፔን ካናሪ ደሴቶች ዳርቻ እንዳዳነ የአደጋ ጊዜ ማእከል አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ከ140 በላይ ስደተኞችን በስፔን ካናሪ ደሴቶች ዳርቻ እንዳዳነ የአደጋ ጊዜ ማእከል አስታወቀ "የካናሪ ደሴቶች የነፍስ አድን አገልግሎት ሰራተኞች እና የቀይ መስቀል ሐኪሞች በሁለት ጀልባዎች የመጡ 142 ስደተኞችን ረድተዋል" ሲል የካናሪ ደሴቶች የደህንነት እና የድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል አርብ ዕለት አስታውቋል። “አነስተኛ የጤና ችግር ያለባቸው” 11 ስደተኞች ወደ አቅራቢያ ሆስፒታሎች መወሰዳቸውን አክሏል። እ.አ.አ. በ2024 የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከ5,000 በላይ ስደተኞች በባህር ወደ ስፔን ለመግባት ሲሞክሩ መሞታቸውን የገለፀው የስደተኞች መብት ተሟጋች ቡድኑ ካሚናንዶ ፍሮንቴራስ ይህም በቀን 33 ሰዎች ይሞታሉ ማለት እነደሆነ ባሳለፍነው ወር አስታውቋል። ከእነዚህ ውስጥ 4,800 ያህሉ የካናሪ ደሴቶችን ለመድረስ ሲሞክሩ ሞተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0