ቱርክ በሶማሊያ የነዳጅና ጋዝ ፍለጋ ልትጀምር እንደሆነ ተገለፀ

ሰብስክራይብ
ቱርክ በሶማሊያ የነዳጅና ጋዝ ፍለጋ ልትጀምር እንደሆነ ተገለፀ ቱርክ እና ሶማሊያ በደረሱት ስምምነት መሰረት የቱርክ መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ቲ.ፒ.ኤ.ኦ (TPAO) በሶማሊያ በሚገኙ ሶስት ብሎኮች የመሬት ጥናት እንደሚያካሂድ የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር አስታውቀዋል። ባይራክታር "ሶማሊያ በጠረፍ ዳርቻ አካባቢ በጣም ጠቃሚ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቶች እንዳላት እናምናለን። ስምምነታችንን የፈረምነው በሶማሊያ የጠረፍ ዳርቻ አካባቢ በሚገኙ 3 ብሎኮች ላይ ነው [...] ቱርክ በነዚህ ሶስት ብሎኮች ለብቻዋ የማሰስ መብት ተሰጥቷታል፤ ፍለጋችን ተሳክቶ ነዳጅ እናመርታለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል። የእያንዳንዱ ብሎክ ስፋት 5,000 ኪሎ ሜትር እንደሆነና ሁለቱ ብሎኮች ከባህር ዳርቻ 50 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ሲገኙ ሶስተኛው ብሎክ ደግሞ ከባህር ዳርቻ 100 ኪሎ ሜትር እርቆ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ አክለውም “በመስከረም መጨረሻ ወይም በጥቅምት ወር መጀመሪያ የቱርክ ኦሩክ ሪስ መርከብን ወደ ክልሉ እንልካለን" ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0