የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የደቡብ ኪቩ ገዥ በግዛቱ የሚካሄደውን የማዕድን ማውጣት ስራ አስቆሙ

ሰብስክራይብ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የደቡብ ኪቩ ገዥ በግዛቱ የሚካሄደውን የማዕድን ማውጣት ስራ አስቆሙ ኩባንያዎችና ኦፕሬተሮች የማዕድን ስፍራዎችን ለቀው እንዲወጡም መመሪያ ሰጥተዋል። ገዥው ዣን ዣክዊ ፑሩሲ ሳዲኪ ዝርዝሮችን ሳይሰጡ እገዳው "ማዕድን ኦውጪዎች በፈጠሩት ውዝግብ" ምክንያት የተወሰነ እንደሆነ ገልፀው ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ በስራ ላይ እንደሚውል ተናግረዋል፡፡ "ሁሉም ድርጅቶች፣ ቢዝነሶች እና የህብረት ስራ ማህበራት በ72 ሰዓት ውስጥ ከማእድን ማውጫ ስፍራዎች እና ስራ ቦታቸው መውጣት አለባቸው" ብለዋል። ውሳኔው በክልሉ ቀዳሚ አምራቾች የሆኑትን እንደ ወርቅ እና የቆርቆሮ የብረታ ብረት ማእድናትን የሚያወጡ አንስተኛ ደረጃ የማእድን አውጪዎችን በእጅጉ ይነካል። በሌላ ማስታወቂያ ገዥው ሁኔታውን ለመገምገም ሐምሌ 23 ከማዕድን ኦፕሬተሮች ጋር ስብሰባ መጥራታቸው ተዘግቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0