የሐምሌ 12 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 12 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ከሩሲያ ጋር ያላት ትብብር ለቶጎ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ዱሴይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። 🟠 ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ የማምረት አቅም ለበርካታ ዓመታት ሲያሽቆለቁል በመቆየቱ መንግሥታቸው ደቡብ አፍሪካን በድጋሚ ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ የስራ እድል ለመፍጠር እንዳሰበ ገልፀዋል፡፡ 🟠 በናይጄሪያ ዝቅተኛው የወር ደመወዝ ወደ 70,000 ናይራ (44 ዶላር) ከፍ ማለቱን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት አማካሪ አስታውቀዋል። 🟠 የኬንያ መንግስት የተቃውሞ ሰልፎች እንዲቆሙ በድጋሚ የጠየቀ ሲሆን ፖሊስ በማእከላዊ ናይሮቢ የሚደረጉ ሰልፎችን ለማገድ ሞክሯል፡፡ 🟠 የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ 99.18% ድምጽ በማግኘት ለአራተኛ ጊዜ በድጋሚ መመረጣቸውን ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ 🟠 ቤልጎሮድ ክልል ሼቤኪኖ ከተማ የኪዬቭ ጦር ባደረሰው ጥቃት አንድ ሰው እንደቆሰለና ሰባት የግል ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። 🟠 የዩክሬን ሃይል ሉሃንስክ ውስጥ ሶስት የአሜሪካ አታካም ሚሳኤሎችን እንደተኮሰ ተዘግቧል። 🟠 ትራምፕ በህዳር ወር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ለመወዳደር መስማማታቸውን ገልጸዋል። 🟠 ባይደን ካማላ ሃሪስ በፕሬዝዳንታዊ ፉክክሩ የሚተኳቸው ከሆነ ምርጫውን የማሸነፍ እድላቸውን በተመለከተ የአሜሪካውያንን አመለካከት ለማወቅ ጥናት እንዲደረግ ማዘዛቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 አርብ ጠዋት ዋና ዋና የአሜሪካ አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ እንቅስቃሴ መቆራረጥ ገጥሟቸው በረራዎችን ለግዜው እንደሰረዙ አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0