ቤላሩስ የትራክተር ኤክስፖርቷን ወደ አፍሪካ አዞረች፦ አፍሪካ ሀገራት የቤላሩስ የእርሻ ማሽነሪዎችን ይፈልጋሉ?

ሰብስክራይብ
ቤላሩስ የትራክተር ኤክስፖርቷን ወደ አፍሪካ አዞረች፦ አፍሪካ ሀገራት የቤላሩስ የእርሻ ማሽነሪዎችን ይፈልጋሉ? ከዓለም ቀዳሚ የትራክተር አምራች ሃገራት አንዷ ቤላሩስ የአውሮፓ ህብረት ከሳምንታት በፊት የትራክተር ኢምፖርቷን ማገዱን ተከትሎ የግብርና ማሽነሪዎቿን ወደ አፍሪካ አህጉር ለመላክ ማቀዷን አስታውቃለች። ይሁን እንጂ የቤላሩስ መንግስት የሚልከውን ምርት ወደ አፍሪካ ሀገራት ለማዘዋወር የወሰነበት ምክንያት የአውሮፓ ህብረት እገዳ ብቻ አይደለም። የአፍሪካን የቤላሩስ ቴክኖሎጂ ፍላጎት በተመለከተ አንዳንድ እውነታዎች፦ 🟠 ሚያዝያ ወር 2024 የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አፍሪካ የምግብ ዋስትናን እንድታሳካ መደገፍ የሚቻልበትን መንገድ ለቤላሩስ የኢንዱስትሪ ተወካዮች አብራርተዋል። በአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የቤላሩስ የእርሻ ማሽነሪ ማምረቻዎችን እና የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎችን የመገንባት ሐሳብ አቅርበዋል። 🟠 መስከረም ወር 2023 ሚንስክ ትራክተር ስራዎች እና የኢትዮጵያ መንግስት የቤላሩስ ማሽኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካን በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር እንደገና ለማስጀመር ንግግር ጀምረዋል። 🟠 የቤላሩስ የማሽን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በግንባታ ላይ ይገኛል። 🟠 ሱዳን፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ዚምባብዌ እና ናይጄሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ የቤላሩስ ትራክተሮችን የሚገዙ ሀገራት ናቸው። ሱዳን ውስጥ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ የመገንባት ሃሳብ ሂደት ላይ ነው። 🟠 ቤላሩስ ዚምባብዌ በስንዴ ምርት ራሷን እንድትችል እረድታለች። በግብርና ሜካናይዜሽን ዘርፍ የጋራ ፕሮጀክት በ2023 ሀራሬ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ለውጭ ገበያ መላክ ችላለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0