የሐምሌ 10 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 10 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በርካታ ጉዳዮችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፦ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ታይቶ የማይታወቅ ግጭት በአብዛኛው አሜሪካ በቀጠናው የምትከተለው ፖሊሲ ውጤት ነው። ሩሲያ ፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል መሆኗን ትደግፋለች። ሉዓላዊነቷ 150 በሚጠጉ ሀገሮች እውቅና አግኝቷል። ሞስኮ በጋዛ ውስጥ በሚገኙ ቡድኖች ላይ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ ሁሉም የውጭ ተዋናዮች ጋር ውይይት ለማካሄድ ያቀረበችው ሀሳብ አሁንም እንደፀና ነው። 🟠 95 የሩሲያ የጦር ምርኮኞች በኪዬቭ ቁጥጥር ስር ከሆኑ ግዛቶች ከ95 የዩክሬን የጦር እስረኞች ጋር በተደረገ የምርኮኞች ልውውጥ እንደተመለሱ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 የአውሮፓ ፓርላማ ከድህረ ምርጫ በኋላ ባሳለፈው የመጀመሪያ ውሳኔ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ለሰላም ተልዕኮ ወደ ሩሲያ ያደረጉትን ጉዞ አውግዟል። 🟠 የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ከህብረቱ ፈንድ 4.2 ቢልዮን ዩሮ ለዩክሬን በየሶስት ወሩ የሚሰጥ የማክሮ ፋይናንስ እርዳታን ወጪ እንዲያደርግ ሀሳብ አቀረበ። 🟠 ቻይና ዋሽንግተን ለታይዋን በምትሸጠው የጦር መሳሪያ ምክንያት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የነበራትን የጦር መሳርያ ቁጥጥር እና ያለመስፋፋት ምክክር ማቋረጧን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0