ታንዛኒያ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር በ2030 3 ሚሊየን ቶን የእህል ማከማቻ አቅም እንዲኖራት አቅዳለች

ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር በ2030 3 ሚሊየን ቶን የእህል ማከማቻ አቅም እንዲኖራት አቅዳለች ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የብሔራዊ የምግብ ክምችት ኤጀንሲ በመጪዎቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ የእህል ማከማቻ አቅሙን ወደ ሶስት ሚሊዮን ቶን እንዲያሰፋ መመሪያ ሰጥተዋል። ይህ ትልቅ ግብ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንቱ በካታቪ ክልል ምፓንዳ ከተማ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ አዳዲስ ዘመናዊ ጎተራ እና መጋዘኖችን ሲጎበኙ ነው። “ይህ 14 ቢሊዮን የታንዛኒያ ሽልንግ (5.2ሚ ዶላር) የሚያወጣ ፕሮጀክት ሀገሪቱ የምግብ ዋስትና ችግር ለመፍታት እና በድህረ ምርት ወቅት የሚደርሰውን ኪሳራ ለመቀነስ ይረዳታል” ሲሉ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የማከማቻ ፋሲሊቲው ማስፋፊያ የታንዛኒያ መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ለማጠናከርና ከእጅ ወደ አፍ ግብርና ወደ ንግድ ግብርና ለመሸጋገር የሚያደርገው ጥረት አካል ነው። ፕሬዝዳንቷ የግብርና ሚኒስቴሩ በጀት በ2020 ከነበረበት 460 ቢልየን ሽልንግ (172 ሚልየን የአሜሪካ ዶላር) ባለፉት ሦስት በጀት ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ አድጎ ከ2021/22 460 ቢልየን ሽልንግ (172 ሚልየን የአሜሪካ ዶላር) በዘንድሮ የበጀት ዓመት 1.248 ትሪሊየን ሽልንግ (467 ሚልየን ዶላር) መድረሱን አመልክተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0