ኮትዲቯር ህጻናትን ከወባ በሽታ ለመጠበቅ የሚያስችል የመጀመሪያውን የወባ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች

ሰብስክራይብ
ኮትዲቯር ህጻናትን ከወባ በሽታ ለመጠበቅ የሚያስችል የመጀመሪያውን የወባ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች ሰኞ እለት የጀመረው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ከአምስት ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ሶስት ህፃናትን ጨምሮ በየቀኑ አራት ሰዎችን ከሚቀጥፈው የወባ ትንኝ ተላላፊ በሽታ ህፃናትን ለመጠበቅ ያለመ ነው። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር መጨረሻ 656,600 ክትባቶችን ከተረከበ በኋላ የህፃናት የፀረ-ወባ ክትባቱን በብሔራዊ የክትባት መርሐግብር ውስጥ አካቷል። በአራት ዙር የሚካሄደው ክትባት በስድስት፣ ስምንት፣ ዘጠኝ እና 15 ወራት እድሜ ውስጥ ላሉ ህፃናት በነጻ ይሰጣል። "ይህ ውሳኔ ልጆቻችንን ከዚህ በሽታ በመጠበቅ ረገድ ትልቅ እርምጃ ነው" ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ፒየር ዲምባ ተናግረዋል። በኮትዲቯር በ2018 ከ1000,000 ህጻናት 49ኙ በወባ በሽታ ይሞቱ የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2021 ወደ 19 ቢቀንስም በሽታው አሁንም ከፍተኛ የጤና ስጋት እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ይገልፃሉ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0