ግብፅ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024-2025 በ1.2 ቢሊየን ዶላር ወጪ 110 የነዳጅ ጉድጓዶችን ለመቆፈር አቅዳለች።
የፔትሮሊየምና ማዕድን ኃብት ሚኒስትሩ ካሪም ባዳዊ የአዲሱን መንግሥት ፕሮግራም በሚመረምረው የፓርላማ ኮሚቴ እንደገለጹት፤ ይህ ትልቅ ዕቅድ የግብፅን የኃይል ነፃነት ለማረጋገጥ እና ለኃይል ማመንጫ አስፈላጊ የሆኑ የነዳጅ አቅርቦቶችን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
ባዳዊ እ.አ.አ በ2030፤ 586 የሚደርሱ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓዶች ለመቆፈር 7.2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ያለመውን የረጅም ጊዜ እቅዳቸውን አስረገጠው ተናግረዋል።
"በተጨማሪም በግብፅ 'ኤክስፕሎሬሽን እና ፕሮዳክሽን ጌትዌይ ' በኩል አለም አቀፍ ጨረታዎችን ያወጣን ሲሆን፤ ይህም አጋሮቻችን አመቱን ሙሉ አዳዲስ የአሰሳ ቦታዎችን መረጃ በዲጂታል መንገድ እንዲያስሱ ማድረግ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናገረዋል።
የግብፅን ኢኮኖሚ ለማጎልበት የነዳጅ እና ጋዝ ወሳኝ ያለውን ወሳኝ ሚና በመግለጽ " ዋናው ተግባራችን ከኤሌክትሪክ እና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር የኃይል ማሰራጫ ጣቢያዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል አስፈላጊውን የነዳጅ አቅርቦት ማቅረብ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።
መንግስት ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ይህም ከውጭ አጋሮች ጋር የጊዜ ሰሌዳ በማስቀመጥ እና ክፍያዎችን በመክፈል፣ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲኖር ማበረታታቻዎች እንዲሰጡ እና የነዳጅ ና ጋዝ ምርቶችን ማፋጠንን ይጨምራል።
"የአየር ንብረት እርምጃ እና የኃይል ሽግግር ለግብፅ ዘላቂ ልማት ስትራቴጂ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሚኒስቴሩ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አካባቢያዊ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ለማስገባት ጥረት ያደርጋል" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240716/5677.html
ግብፅ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024-2025 በ1.
ግብፅ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024-2025 በ1.
Sputnik አፍሪካ
ግብፅ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024-2025 በ1.2 ቢሊየን ዶላር ወጪ 110 የነዳጅ ጉድጓዶችን ለመቆፈር አቅዳለች። የፔትሮሊየምና ማዕድን ኃብት ሚኒስትሩ ካሪም ባዳዊ የአዲሱን መንግሥት ፕሮግራም በሚመረምረው የፓርላማ ኮሚቴ እንደገለጹት፤ ይህ ትልቅ... 16.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-16T17:06+0300
2024-07-16T17:06+0300
2024-07-16T17:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий