ቡርኪናፋሶ የጦር መሳሪያዎችን ለUገሪቱ ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሀገራት ኩባንያዎች፤ የሰጠችውን የማዕድን ማውጣት ፍቃድ ልትሰርዝ ነው።

ሰብስክራይብ
ቡርኪናፋሶ የጦር መሳሪያዎችን ለUገሪቱ ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሀገራት ኩባንያዎች፤ የሰጠችውን የማዕድን ማውጣት ፍቃድ ልትሰርዝ ነው። ይህንን ያስታወቁት የሀገሪቱ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ለህባቸው ባደረጉት ንግግር ነው። "አንዳንድ [ሀያላን] ለእኛ (ወታደራዊ) መሳሪያዎችን ለመሸጥ ፍቃደኛ አይደሉም፤ ከተወሰኑ ሀገራት የገዛናቸውን መሳሪያዎች አግደውብናል ምክንያቱም የተወሰኑ የመሳሪያ ክፍሎችን ለማምረት ፍቃድ ስላላቸው ነው፤ እነዚህ ሀገራት ግን የጦር መሳሪያ ለማምረት የሚያስችላቸውን ማዕድናት የሚያገኙት ከቡርኪናፋሶ ነው" ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራኦሬ አክለውም ገልፀዋል። " ሕዝቡም “ይህ ሊቆም ይገባል ” በማለት በደስታ ተናግረዋል። " የእነዚህን የማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ፍቃዶች እንሰርዛለን፤ የማዕድን ሀብታችንን እየበዘበዛችሁ የጦር መሳሪያ አልሸጥም ማለት አትችሉም። " "እኛ እራሳችን እንበዘብዛቸዋለን" ሲሉ ውሳኔያቸውን አስታውቀዋል። ነገረ ግን የትኛውን ሀገር እንዳስጠነቀቁ አልተገለጸም። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0