የሳህል ሀገራትን ሰላም ማስጠበቅ የነዋሪዎቿ ኃላፊነት እንደሆነ ሞስኮ ታምናለች

ሰብስክራይብ
የሳህል ሀገራትን ሰላም ማስጠበቅ የነዋሪዎቿ ኃላፊነት እንደሆነ ሞስኮ ታምናለች “በሰሃራ-ሳህል አካባቢ ያለውን ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ በዋናነት የህዝቡ ሥራ ነው። እዚህ ላይ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በማሊ፣ በኒጀር እና በቡርኪናፋሶ መካከል የተፈረመው" የሊፕታኮ-ጎርማ ቻርተር "ነው፡፡ ሀገራቱ በመከላከያ እና ሽብርተኝነት በጋራ ለመመከት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው ሲሉ በመንግስታቱ ድርጅት የሩሲያ ምክትል ቋሚ ተወካይ አና ኢቭስቲኒቫ ተናግረዋል። አክለውም ይህ በደህንነት እና በልማት መስክ የተፈጠረ መሠረታዊ አወቃቀር ነው፡፡ ሩሲያ ለሳህል ሕብረት ሀገራት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ሥምምነት መሠረት ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች፣ ይህም የሕብረቱ ሀገራትን ብሔራዊ የጦር ኃይል የውጊያ አቅም ማሳደግ እና ሰብአዊ ድጋፍ መሥጠትን ይጨምራል ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0