ቤሎሶቭ እና ኦስቲን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ቤሎሶቭ እና ኦስቲን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ "እ.ኤ.አ ሐምሌ 12 ቀን 2024 በሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በሩሲያ  አነሳሽነት የስልክ ውይይት አካሂደው ነበር" ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው ገልጾ ሁለቱ ወገኖች በመከላከያ ጉዳዮች ፣የደህንነት ስጋቶች በመቀነስ ዙሪያ እና ግጭቶች እንዳይስፋፉ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። የፔንታጎን ምክትል የፕሬስ ፀሐፊ ሳብሪና ሲንግ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ባለሥልጣናቱ በስልክ መወያየታቸውን  አረጋግጠዋል። "በስልክ ውይይታቸው ወቅት የመከላከያ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን ግጭት ውስጥ በሆነችበት ወቅትም ቢሆን ግንኙነት የማድረግ አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው መነጋገራቸውን" ሲንግ ተናግረዋል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.ኤ.አ ሰኔ 25 እንደሆነ ተገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0