ኒጀር እና ቻድ የኒጀር-ቻድ-ካሜሩን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክትን እንደገና እንዳስጀመሩና የነዳጅዘይት አቅርቦት ውላቸውን እንዳደሱ ተሰማ

ሰብስክራይብ
ኒጀር እና ቻድ የኒጀር-ቻድ-ካሜሩን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክትን እንደገና እንዳስጀመሩና የነዳጅዘይት አቅርቦት ውላቸውን እንዳደሱ ተሰማ በቻድ የዘይት፣ ማዕድን እና ስነ-ምድር ሚኒስትር ንዶሌኖድጂ አሊክስ ናይምባዬ የተመራ የልዑካን ቡድን ከረቡዕ ጀምሮ በኒጀር የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑን ሚዲያዎች ዘግበዋል። ጉብኝቱ የኒጀር-ቻድ-ካሜሩን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክትን እንደገና ለማስጀመርና የነዳጅዘይት አቅርቦት ውላቸውን ለማዳስ ያለመ እንደሆነ ታውቋል። የቧንቧ መስመሩ ስራ መጀመር በቻድ በኩል ከኒጀር ወደ ካሜሩን ድፍድፍ ዘይት ለመላክ ያስችላል ሲል ዘገባው አመልክቷል። ፕሮጀክቱ የሶስቱን ሀገራት ኢኮኖሚ እንደሚያሳድግ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የስራ እድሎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል። የነዳጅዘይት አቅርቦት ውሉ እድሳት በቻድ በተመጣጣኝ ዋጋ የተረጋጋ የናፍጣ አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0