ሞስኮ በጋራ የአውሮፕላኖች ምርት የቤላሩስን ተሳትፎ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

ሰብስክራይብ
ሞስኮ በጋራ የአውሮፕላኖች ምርት የቤላሩስን ተሳትፎ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች በአውሮፕላን ኢንዱስትሪ ከሚንስክ ጋር መተባበር ሩሲያ ወዳጅ ካልሆኑ ሀገራት የሚመጡ ምርቶችን የመተካት ችግሮችን ለመፍታት ይረዳታል ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚክሂል ጋሉዚን ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ቤላሩስ አስፈላጊው የምርት መሰረት እና የሰው ኃይል እንዳላትም ገልጸዋል፡፡ "በአውሮፕላን ግንባታ ላይ ከቤላሩስ አጋሮች ጋር ግኑኝነት መፍጠር ወዳጅ ካልሆኑ ሀገራት የሚመጡ የውጭ ምርቶችን የመተካት ችግሮችን ለመፍታት እና በመጨረሻም ደህንነቱ የተጠበቀ እና በውጭ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ የአቪዬሽን መሳሪያዎችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ምንም ጥርጥር የለውም" ብለዋል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0