ኢራን የብሪክስ የክፍያ ስርዓት ይዋሃድ ስትል ሀሳብ አቀረበች። የምዕራባውያንን የበላይነት መገዳደር?

ሰብስክራይብ
ኢራን የብሪክስ የክፍያ ስርዓት ይዋሃድ ስትል ሀሳብ አቀረበች። የምዕራባውያንን የበላይነት መገዳደር? የሩሲያ ሚር እና የኢራን ሼታብ የክፍያ ስርዓቶች የተሳካ ውህደት ያነቃቃው የኢራን ተነሳሽነት ለአባል ሀገራቱ እንዲሁም በአጠቃላይ ለቡድኑ ጥቅም እንዳለው ኢራናዊው የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ባለሙያ አሊሬዛ ሞሀመዲ አብራርተዋል። "ንግድን ማበረታታት፣ የኢኮኖሚ አስተዳደር፣ የመገበያያ መረጋጋት፣ የብሪክስ ኢኮኖሚዎችን ማፅናት፣ ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ሌሎች ሀገራትን መቀበል፣ ለብሪክስ ልማት ባንክ መንገድ መጥረግ፣ የተዋሃደ የብሪክስ ገበያን መፍጠር እና የብሪክስ መገበያያን ማቆም ከጥቅሞቹ መካከል ናቸው" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የምዕራባውያን ኢኮኖሚ ከ2008ቱ የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ለዩናይትድ ስቴትስ መሩ የኢኮኖሚ ሥርዓት ተገቢ አማራጭ ማቅረብ እንዳልቻለ የጠቆሙት ኤክስፐርቱ “ቀውሶቻቸውን እያደጉ ላሉ ሀገራት መላክና በነዚሁ የዓለም ክፍሎች ሽብርተኝነትን ማበረታታት መርጠዋል” ብለዋል። የምዕራባውያን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በዝባዥ ነው ሲሉ ተችተው የአፍሪካ ታዳጊ ሀገራት የሚያጋጥማቸውን ተደጋጋሚ ፈተና አንስተዋል። በተቃራኒው የብሪክስ ትብብር ለአፍሪካ ሀገራት ሊያመጣ የሚችለውን ጥቅም ጠቅሰዋል። "ይህ አፍሪካ ሀገራት እንዲነሳሱና ድርሻቸውን መጠቀም እንዲችሉ የሚያደርግ ትልቅ እድል ነው" ሲሉ ሞሀመዲ አፅንዖት ሰጥተዋል። እንደ ሞሀመዲ ገለጻ ምዕራባውያን ሀገራት የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት ሽግግር የበላይነታቸውን ያዳክማል በሚል ይሰጋሉ። "ነገር ግን ያላቸው አማራጭ ፍትሃዊ የሆነ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሥርዓትን ተቀብሎ በሽግግሩ ላይ መሳተፍ ብቻ ነው" ሲሉ አጠቃለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0