የካሜሩን ህግ አውጪዎች የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫዎችን እስከ 2026 ድረስ የሚያራዝም ረቂቅ ህግ አጸደቁ

ሰብስክራይብ
የካሜሩን ህግ አውጪዎች የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫዎችን እስከ 2026 ድረስ የሚያራዝም ረቂቅ ህግ አጸደቁ የህግ አውጭዎችን ስልጣን እስከ መጋቢት 2026 ለአንድ ዓመት የሚያራዝመውን ረቂቅ ህግ ገዥው የካሜሩን ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ሲ.ፒ.ዲ.ኤም) በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። በእርምጃው መሰረት የሕግ አውጭ እና የአካባቢ ምርጫ ጥቅምት 2025 ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኋላ ይካሄዳል። መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት ሊደረጉ የታቀዱ አራት ምርጫዎችን የሚያካትተውን “የምርጫ ካላንደር ማቃለል” አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ ለምርጫው መዘግየት ምክንያት አቅርቧል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን የምርጫው መዘግየት በመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ፖል ቢያን የመፎካከር እድላቸውን ያዳክማል በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል። በሚቀጥለው ዓመት የህግ አውጭ እና የአካባቢ ምርጫውን ማካሄድ ከፕሬዝዳንታዊ ድምጽ አሰጣጥ በፊት መነቃቃትን ይፈጥርልን ነበር ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ሞግተዋል። የካሜሩን የምርጫ ህግ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች በፓርላማ ወይም በአካባቢ ምክር ቤቶች ውክልና ባለው ፓርቲ ወይም ከበርካታ ባለስልጣናት በሚገኝ ድጋፍ እንዲታጩ ያስገድዳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0