የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የቆየ የእረኞችና ገበሬዎች ግጭትን ለማስቆም የእንስሳት ሀብት ልማት ሚኒስቴር አቋቋሙ

ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የቆየ የእረኞችና ገበሬዎች ግጭትን ለማስቆም የእንስሳት ሀብት ልማት ሚኒስቴር አቋቋሙ በእንስሳት ሀብት ማሻሻያ ዙርያ የተቋቋመው ፕሬዝዳንታዊ ኮሚቴ ምረቃ ላይ ይፋ የተደረገው እርምጃ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በጉዳዩ ላይ ብቻ ያተኮረ ሚኒስቴር ይህንን አንገብጋቢ ጉዳይ ለመቅረፍ እና የእንስሳትን እምቅ አቅም መጠቀም በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ያሳየ ነው። "መፍትሄው እሩቅ ነው ያለው ማነው? እኔ "መፍትሄው ቅርብ ነው" እላለሁ። ብዙዎቻችሁ ጥሩ ልምድ አላችሁ ናይጄሪያም እንድትበለፅግ ትፈልጋላችሁ" ሲሉ በስብሰባው ተናግረዋል። "ናይጄሪያ በከብት እርባታ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማስቻል፣ ለዓመታት ላስጨነቀን ለዚህ ችግር መፍትሄ እና እድል አግኝተናል፣ እናም ብልጽግና በእጃችን ነው ብዬ አምናለሁ።" ተነሳሽነቱ የሀገር አቀፍ የእንስሳት ማሻሻያ ኮንፈረንስ እና 21 የውሳኔ ሃሳቦችን ያካተተ ሪፖርትን ጨምሮ ለአንድ ዓመት ሲካሄድ የቆየ ሂደት ውጤት ነው። በአየር ንብረት ለውጥ እና የግብርና መስፋፋት በመሳሰሉት ምክንያቶች የተነሳ በእረኞች እና ገበሬዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በብዙ የናይጄሪያ አካባቢዎች አሳዛኝ የህይወት መጥፋት እና አለመረጋጋት አስከትሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0