ሩሲያ እና ሞዛምቢክ በኃይል ኢንዱስትሪ ትብብር ስለመጀመር ተወያዩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ሞዛምቢክ በኃይል ኢንዱስትሪ ትብብር ስለመጀመር ተወያዩ ጉዳዩ በሩሲያ ፌዴራላዊ ማዕድን ሀብት ኤጀንሲ (ሮስኔድራ) ሀላፊ ኢቭጌኒ ፔትሮቭ እና የሞዛምቢክ የህዝብ ስራዎች፣ ቤቶች እና የውሃ ሀብቶች ሚኒስትር ካርሎስ ሜስኪታ መካከል በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተነስቷል። "በስብሰባው [የሩሲያ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ] ሩስሃይድሮ ቡድን ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ መንግሥት እንዲሁም በኤሌክትሪክ ሃይል ኢንዱስትሪ ውስጥ ካሉ የመንግስት ድርጅቶች እና ልዩ ኩባንያዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማነቃቃት በሚቻልበት ጉዳይ ውይይት ተደርጓል" ሲል ሮስኔድራ በመግለጫው አስታውቋል። በየካቲት ወር በሞዛምቢክ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ሱሪኮቭ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሁለቱ ሀገራት በኢነርጂ እና ውሃ ሃይል ዘርፎች ተባብረው ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት የሩስያ የግንባታ ኩባንያ ኢንተር ራኦ እና ኤሌክትሪካዴድ ደ ሞዛምቢክ የ120MW ሉሪዮ-2 የውሃ ኃይል ማመንጫን ሞዛምቢክ ውስጥ ለመገንባት ስምምነት መፈራረማቸውን የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0