ሩሲያ እና ህንድ በውይይት እና በዲፕሎማሲ የዩክሬንን ግጭት ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እንደሚገባ አንዳሳሰቡ ናሬንድራ ሞዲ እና ቭላድሚር ፑቲን ያወጡት የጋራ መግለጫ አመልክቷል

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ህንድ በውይይት እና በዲፕሎማሲ የዩክሬንን ግጭት ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እንደሚገባ አንዳሳሰቡ ናሬንድራ ሞዲ እና ቭላድሚር ፑቲን ያወጡት የጋራ መግለጫ አመልክቷል የሰነዱ ሌሎች ቁልፍ ነጥቦች፡- 🟠 መሪዎቹ በሀገሮቻቸው መካከል ያለውን የስትራቴጂካዊ አጋርነት አቅም በተሟላ መልኩ እውን ለማድረግ ሁሉንም ጥረት ያደርጋሉ። 🟠 የሩሲያ-ህንድ ግንኙነት ውስብስብ እና ባልተረጋገጠ ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ የተረጋጋ ሆኖ ይቆያል። 🟠 ሁለቱ ሀገራት በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ እና በህዋ ኢንዱስትሪ ያላቸውን ትብብር ያጠናክራሉ፡፡ 🟠 የኢነርጂ ዘርፍ ትብብር የኒውክሌር ኢነርጂ እና የዘይት ማጣሪያን ጨምሮ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። 🟠 የሁለትዮሽ ንግዳቸውን ሚዛናዊ ለማድረግ ህንድ ወደ ሩሲያ የምትላካቸውን ምርቶች ለመጨመር አቅደዋል፡፡ 🟠 የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከርም ተስማምተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0