የዚምባብዌ ኩባንያ እሴት በመጨመር ሊቲየም ባትሪ ለማምረት እንቅስቃሴ ጀምሯል።

ሰብስክራይብ
የዚምባብዌ ኩባንያ እሴት በመጨመር ሊቲየም ባትሪ ለማምረት እንቅስቃሴ ጀምሯል። የፕሬዚዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ እሴት መጨመር፤ ከሰፊው የሀገሪቱ የማዕድን ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ቬሪፊ ኢንጂነሪንግ የተሰኘው የሀገሪቱ ኩባንያ ወደ ሊቲየም ባትሪ ማምረት ገብቷል። በአፍሪካ ትልቁ የሊቲየም ክምችት እንዳላት የሚነገረው ዚምባብዌ በቅርቡ በኮንትሮባንድ ምክንያት 1.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ በማሳየቷ ጥሬ ሊቲየም ወደ ውጭ መላክን አግዳለች። እ.አ.አ በ 2005 በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመው መንግስታዊው ቬሪፋይ ኢንጂነሪንግ በዚምባብዌ የቴክኖሎጂ እድገት አበርክቶ ላይ ትልቅ ታሪክ ያለው ኩባንያ ነው። ኩባንያው ኦክስጂን በማምረት እንደ ሞዛምቢክ ላሉ ጎረቤት ሀገራት በመላክ የሚታወቅ ነው። "አሁን አዳዲስ ስራዎችን በመስራት ላይ ነን፤ አሁን ሊቲየም ባትሪ ለማምረት እንቀስቃሴ ጀምረናል። በእርግጥ ገና ጅምር ላይ ነው፤ ነገር ግን ሊቲየም ባትሪዎች በማምረት፤በመጨረሻም ለኤሌክትሪክ መኪና የሚሆኑ ባትሪዎች ማምረት እንፈልጋለን"ሲሉ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ቋሚ ፀሃፊ ፋኑኤል ታግዊራ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0