የማሊ ፕሬዝዳንት የሣህል ሀገራት ህብረት መሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የኒያሚ መግለጫን ግልባጭ ይፋ አደረጉ

ሰብስክራይብ
የማሊ ፕሬዝዳንት የሣህል ሀገራት ህብረት መሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የኒያሚ መግለጫን ግልባጭ ይፋ አደረጉ ለማስታወስ ያህል፣ ትናንት ይፋ የተደረገው የመሪዎች ጉባኤው ዋና ዋና ነጥቦች ጥቂቶቹን እነሆ፡- ኮንፌዴሬሽኑ በቡርኪናፋሶ፣ በማሊ እና በኒጀር ሀገራት የተመሰረተ ነው። ማሊ የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽንን ለአንድ አመት በሊቀመንበርነት ትመራለች። የሣህል ሀገራት ሕብረት ኢንቨስትመንት ባንክ እና ለአባል ሀገራት የማረጋጊያ ፈንድ ሊቋቋም ነው። የህብረቱ መሪዎች እንደ ግብርና፣ ውሃ፣ ኢነርጂ እና ትራንስፖርት ባሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች "ሀብትን በማሰባሰብ መሥራት" ይፈልጋሉ። አባል ሀገራቱ የየራሳቸውን ቋንቋዎችን በሀገሮቻቸው የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች የበለጠ ጥቅም ላይ እንዲውል ጥሪ አቅርበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0