የአሜሪካ ሚዲያዎች በኪየቭ አገዛዝ በዶንባስ ነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ያላወቁ መስለው መቅረባቸው "አስቂኝ" ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ።

ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ሚዲያዎች በኪየቭ አገዛዝ በዶንባስ ነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ያላወቁ መስለው መቅረባቸው "አስቂኝ" ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ሩሲያዊ የጦር ምርኮኛ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር። በኪየቭ መንግስት የሚፈፀመው ግፍ ሁሉ ከበፊትም ጀምሮ ይታወቃል ሲሉ ለሩሲያ ሚዲያ በአፅንኦት ተናግዋል። "እነዚህ የአሜሪካ ጋዜጠኞች አንድም ቃል የማይተነፍሱበት የተረጋገጡ እውነታዎች ናቸው"ብለዋል ዲፕሎማቷ። ዛካሮቫ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተደጋጋሚ ሪፖርት ማቅረቡን እና ተመሳሳይ ሰነዶች ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ማሰራጨታቸውንገልጸው፤ነገር ግን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃ መረጃውን ችላ ለማለት ሁሉንም ነገር አድርገዋል ሲሉ ወቅሰዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0