የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ "የቶማስ ሳንካራ ምትክ ነው" ሲሉ በኒጀር የሚኖሩ የቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ተናገሩ።
ትራኦሬ ባለፈው አርብ የሳህል መንግስታት ህብረት አባል ሀገራት የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት በኒጀር ዋና ከተማ በነበራቸው ቆይታ ከቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ተገናኝተዋል።በስብሰባው በርካታ ቁጥር ያላቸው የቡርኪናቤ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በሽብርተኝነት ላይ እያስመዘገቡ ያሉትን ድሎችን እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እያደረጉ ላሉት ጥረት ተሳታፊዎቹ እንኳን ደስ ያለህ ብለዋቸዋል።
"እርስዎ የቶማስ ሳንካራ ምትክ ኖት ፤ የሳንካራን ራዕይ ለመመለስ እና ቡርኪናፋሶ እንዲሁም አፍሪካ ነፃ ለማውጣት የጀመሩትን ስራ ያጠናቅቃሉ"ሲል ከኮሚኒቲው አባላት አንዱ ተናግሯል።
እ.አ.አ ከ1983 እስከ 1987 የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቶማስ ሳንካራ ብዙ ጊዜ “የአፍሪካ ቼ ጉቬራ” እየተባለ የሚጠራ አብዮታዊ መሪ ነበር። ሙስናን ለመዋጋት፣ በሁሉም መስክ ራስን መቻልን፣ የሴቶችን መብት ማስከበር፣ ጤናና ትምህርትን ማሳደግ እንዲሁም ዋና ዋና የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የአካባቢ ማሻሻያዎችን አድርጓል። የእሱ ውርስ በቡርኪናፋሶ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ ያለው ሲሆን ፤ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለማህበራዊ ፍትህ ዘላቂ መነሳሳትን በአህጉሪቱ እንደለኮሰ ይታመናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240706/5057.html
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ "የቶማስ ሳንካራ ምትክ ነው" ሲሉ በኒጀር የሚኖሩ የቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ተናገሩ።
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ "የቶማስ ሳንካራ ምትክ ነው" ሲሉ በኒጀር የሚኖሩ የቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ተናገሩ።
Sputnik አፍሪካ
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ "የቶማስ ሳንካራ ምትክ ነው" ሲሉ በኒጀር የሚኖሩ የቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ተናገሩ። ትራኦሬ ባለፈው አርብ የሳህል መንግስታት ህብረት አባል ሀገራት የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት በኒጀር ዋና ከተማ... 06.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-06T17:52+0300
2024-07-06T17:52+0300
2024-07-06T18:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ "የቶማስ ሳንካራ ምትክ ነው" ሲሉ በኒጀር የሚኖሩ የቡርኪናቤ ማኅበረሰብ አባላት ተናገሩ።
17:52 06.07.2024 (የተሻሻለ: 18:20 06.07.2024)
ሰብስክራይብ