የሰኔ 28 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 የዩኤስ አፍሪካ ኮማንድ እንዳስታወቀው አሜሪካ ወታደሮቿን ኒጀር ካለው የአየር ጦር ሰፈር የምታወጣበት ቀነ ገደብ እ.አ.አ ሀምሌ 7 ይጠናቀቃል።የኒጀር ባለስልጣናት የቀድሞ የአሜሪካ ጦር ሠፈርን እና መገልገያዎችን ይቆጣጠራሉ።
🟠 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በተቃውሞ ሰልፉ ባስከተለው ቀውስ የተነሳ 47 የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲታጠፉ አዘዙ።በተጨማሪም የመንግስት አማካሪዎች ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ ወስነዋል። የመንግስት የግንባታ ህንፃ እድሳት ወጪዎችም እንዲሁ ይቀንሳሉ ብለዋል።
🟠 ኒጀር የካናዳውን ጎቪኤክስ ኩባንያ የዩራኒየም ማዕድን አውጪ ኩባንያን ፍቃድ ሰርዛለች፤የማዳኦኤላ የማዕድን ማውጫ ቦታን ወደ የህዝብ ንብረትነት አስገብቷል ፤ ኩባንያው ይህንን ውሳኔ ይግባኝ ለማለት አቅዷል።
🟠 በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል በምትገኘው በሰሜን ኪቩ ግዛት በመንግስት ሠራዊት እና በኤም 23 አማፂያን መካከል የተካሄደው ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ከዛሬ አርብ ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ሲል የኮንጎው የዜና ፖርታል አክቱዋላይት ዘግቧል።
🟠 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በዩክሬን ግጭት ማስቆም በሚቻልባቸው መፍትሄዎች ሀሳቦች ላይ ተወያይተዋል።
🟠 ባሳለፍነው ሳምንት የሩስያ ጦር ሃይሎች በዩክሬን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ተቋማት እና በድሮን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ላይ 23 የቡድን ጥቃቶችን ማውደሙን አስታውቋል።
🟠 ሪሺ ሱናክ በፓርላማ ምርጫ ሽንፈትን ተከትሎ የዩናይትድ ኪንግደም ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሥልጣኑን እንደሚለቁ አስታወቀ።
🟠 እ.አ.አ ከ ሐምሌ 9-11 በአሜሪካ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ለዩክሬን አዲስ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን ለማቅረብ እንደሚወስን የሕብረቱ ዋና ፀሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።
🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቅርቡ በጣሊያን በተካሄደው የቡድን 7 ስብሰባ ላይ በእርጅና ሳቢያ እንዲህ መሆናቸው የአውሮፓ መሪዎች አስደንግጧል ሲል ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240705/4997.html
የሰኔ 28 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሰኔ 28 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 28 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የዩኤስ አፍሪካ ኮማንድ እንዳስታወቀው አሜሪካ ወታደሮቿን ኒጀር ካለው የአየር ጦር ሰፈር የምታወጣበት ቀነ ገደብ እ.አ.አ ሀምሌ 7 ይጠናቀቃል።የኒጀር ባለስልጣናት የቀድሞ የአሜሪካ ጦር ሠፈርን እና... 05.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-05T20:17+0300
2024-07-05T20:17+0300
2024-07-05T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий