የሩሲያው የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሜድቬድቭ በ2024 190,000 የሚሆኑ ዜጎች ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ውል መግባታቸውን ገልጸዋል።

ሰብስክራይብ
የሩሲያው የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሜድቬድቭ በ2024 190,000 የሚሆኑ ዜጎች ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ውል መግባታቸውን ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ 2024 190,000 የሚጠጉ የሩሲያ ዜጎች ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ውል የተፈራረሙ ሲሆን፣በየቀኑ አማካይ የምልመላ ቁጥር ወደ 1,000 እንደሚጠጋ ፤የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ሐሙስ ዕለት ተናግረዋል። ወደ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዞን ለመሄድ የወሰኑ ዜጎችን አመስግነው፤ አሁን"በልበ ሙሉነት ወደ ድል እየተቃረብን ነው"በኃላፊነት ስሜት ከልባቸው የሚታገሉትንም ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም አክለዋል።" በታኅሣሥ ወር አጋማሽ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዞን 244,000 የሚጠጉ ወታደሮች መሰማራታቸውን ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0