የሊባኖስ የሺዓ ንቅናቄ ሂዝቦላህ እሮብ እና ሀሙስ የእስራኤልን ዒላማዎች19 ጊዜ መምታቱን ተናግሯል።

ሰብስክራይብ
የሊባኖስ የሺዓ ንቅናቄ ሂዝቦላህ እሮብ እና ሀሙስ የእስራኤልን ዒላማዎች19 ጊዜ መምታቱን ተናግሯል። ሐሙስ እለት ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኙ ሶስት የእስራኤል ዋና መሥሪያ ማዘዣዎች ላይ 200 ሮኬቶችን መተኮሱን ተናግሯል።ከዚያ በኋላም ሰባት የእስራኤል ዋና ማዘዣዎች እና የጦር ሰፈሮችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈጸም ችሏል። የእስራኤል መከላከያ ሃይል በጥቃቱ ወቅት ሂዝቦላህ ወደ 200 የሚጠጉ ሮኬቶችን ወደ ሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል መተኮሱን የዘገበ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ በእስራኤል የአየር መከላከያ ሃይል እና በእስራኤል አየር ሃይል መመታታቸው ተገልጿል። የእስራኤል መከላከያ ሃይል ሰኔ 18 ቀን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ለሚደረገው ጥቃት ተግባራዊ ዕቅዶችን አውጥቶ ማፅደቁን አረጋግጦ ነበር።የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ በኋላ እንደተናገሩት እስራኤል በሂዝቦላህ እና በሊባኖስ ላይ "ያላትን አካሄድ በመለወጥ" ፈጣን ውሳኔ በማሳለፍ፤ ሄዝቦላህ ለመደምሰስ"ሁሉን አቀፍ ጦርነት" ለመግጠም መዛታቸው ይታወሳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0