የሰኔ 27 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
🟠 ቭላድሚር ፑቲን ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ በኋላ ለጋዜጠኞች ንግግር አድርገዋል፡- የዩክሬን ግጭት አፈታት፣ የመካከለኛ እና የአጭር ክልል ሚሳኤሎች ስምሪት እና ከአሜሪካ ጋር መመካከርን የተመለከቱ ጉዳዮች አንስተዋል።
🟠 በሰሜን እስራኤል የሊባኖስ ንቅናቄ ሂዝቦላ የተኮሰውን የሮኬቶች ናዳ ተከትሎ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል። ንቅናቄው ቀደም ሲል በሶስት የእስራኤል ዋና መሥሪያ ቤቶች ላይ 200 ሮኬቶችን ማስወንጨፉን አስታውቋል። የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ኢላማዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።
🟠 ኔቶ የማሪን ለፔን ፓርቲ በምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ ፈረንሳይ ከህብረቱ ወታደራዊ እዝ ልትወጣ ትችላለች የሚል ስጋት እንዳለው የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
🟠 የአሜሪካ ዴሞክራቶች ባይደንን መተካት ስለሚቻልበት መንገድ ሳይሆን ስለ ስልቱ ነው እየተወያዩ ያሉት ሲል የቀድሞ የኦባማ አማካሪ ቫን ጆንስ ተናግሯል። ሁሉም ሰው ያሉትን አማራጮች ለመረዳት እየሞከረ እንዳለና ፓርቲው "መጠነ ሰፊ ድንጋጤ" ውስጥ እንደሚገኝ ጆንስ አስታውቋል።
🟠 ከሰኔ 26 ጀምሮ ቼክ ሪፐብሊክ ለሩሲያ ዜጎች የባዮሜትሪክ ፓስፖርቶችን ብቻ እንደምትቀበል እና
ግለሰቦች መደበኛ ፓስፖርት ይዘው በሪፐብሊኩ ውስጥ መገኘት እንደማይችሉ የቼክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
🟠 ፊቷ ላይ ትልቅ የውልደት ምልክት ኖሮባት የተወለደችው አሜሪካዊቷ ሉና ፌነር የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምናዋ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ተጠናቀቀ። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ፊቷ ላይ የነበረው ስፌት ተነስቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240704/4929.html
የሰኔ 27 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
የሰኔ 27 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 27 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ቭላድሚር ፑቲን ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ በኋላ ለጋዜጠኞች ንግግር አድርገዋል፡- የዩክሬን ግጭት አፈታት፣ የመካከለኛ እና የአጭር ክልል ሚሳኤሎች ስምሪት እና ከአሜሪካ ጋር መመካከርን የተመለከቱ... 04.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-04T20:36+0300
2024-07-04T20:36+0300
2024-07-04T21:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий